እንኳን ወደ ጣና ሳተላይት ቴሌቪዥን በደህና መጡ!
የጣና ሳተላይት ቴሌቭዥን፤ የቴሌቪዥን ጣቢያ ብቻ ሳይሆን እንቅስቃሴም ነው ማለት ይቻላል። የዐማራ ማኅበረሰብ ድምጽ ለመሆን፣ የበለፀጉ ታሪካዊ ቅርሶቻችንን ለማስተዋወቅ፣ አንኳር እሴቶቻችንን ለማጠናከር እና በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍና በደል ለወገናችን እና ለመላው ዓለም ለማሳወቅ በሥራ ላይ እንገኛለን። ግባችን የደረሱ እና እየደረሱ ያሉ ጥፋቶችን በማጋለጥ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከጎናችን በመቆም የማኅበረሰባችንን ትግል እንዲደግፍ ማድረግ ነው።
አሳታፊ እና ሃሳብ ቆስቋሽ በሆኑ ይዘቶች የዐማራን ባህል አና ታሪካዊ ቅርሶች በማስተዋወቅ፣ የዐማራ ሕዝብን እሴቶች በማስረፅ እና በማጠናከር፣ የዐማራ ህዝብ እየደረሰበት ያለውን ፈተና እና ኢፍትሃዊነት ግንዛቤ በማስጨበጥ፣ ታሪካችንን ለዓለም በማካፈል የመግባቢያ እና የአብሮነት ድልድዮችን ለመገንባት እንተጋለን ።
ጣና ሳተላይት ቴሌቭዥንን በመቀላቀል ወይም በመደገፍ፤ አኩሪ ታሪካችንን ለመጠበቅ፣ እሴቶቻችንን ለማስከበር እና ለዐማራ ማኅበረሰብ ፍትሕ እና እኩልነት ለመታገል ጉዞ ጀምረናል፤ መጪው ዘመን ብሩኅ እንዲሆን ለማድረግ እንረባረብ።
እንደገና እንኳን ለመላው ዐማራ ድምጽ ወደሆነው፤ የመላውን ዐማራ ያለፈ ታሪክ፣ የዕለት ተዕለት ፈተናዎቻችን እና ስኬቶቻችንን፣ እንዲሁም የወደፊት ተስፋችንን እንደአንድ አንደበት ወደምንናገርበት ወደ ጣና ሳተላይት ቴሌቪዥን በደህና መጡ!
Welcome to Tana Satellite Television!
Tana Satellite Television is not just a channel – it’s a movement. We are here to be the voice of the Amhara community, promoting our rich historical heritage, strengthening our core values, and shedding light on the injustices faced by our people. Our goal is to bring these important issues to the forefront and rally the international community to stand by our side and support our community.
Through engaging programs and thought-provoking content, we aim to showcase and promote Amhara historical properties, instill and strengthen Amhara values, and raise awareness about the challenges and injustices faced by the Amhara people. By sharing our stories with the world, we strive to build bridges of understanding and solidarity that transcend borders.
Join us on Tana Satellite Television as we embark on a journey to preserve our past, uphold our values, and fight for justice and equality for the Amhara community. Together, we can make a difference. Together, we can create a brighter future for all. Welcome to Tana Satellite Television – where every voice matters, every story is heard, and every heart beats as one.